(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 1/2011)ምርጫ 97ን ተከትሎ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች የተፈጸመውን ግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት ያጣራው ኮሚሽን አባላት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያቀረቡት ጥያቄ እስካሁን ተቀባይነት አለማግኘቱን ገለጹ። በስደት ላይ የሚገኙት የኮሚሽኑ የቀድሞ አመራሮች ከመቶ ዘጠና ዘጠኝ በላይ ሰዎች የተገደሉበትንና ከ30ሺ በላይ ሰዎች በጅምላ የታሰሩበትን እውነተኛ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማቅረብ ቢጠይቁም በመንግስት በኩል ምላሽ አላገኙም። የኮሚሽኑ አባላት እውነተኛውን ሪፖርት በወቅቱ እንዳያቀርቡ በመታገዳቸውና የግድያ ዛቻ ስለደረሰባቸው ከሃገር ተሰደው መቆየታቸው ይታወሳል። እናም ምርጫ 97ን ተከትሎ በተወካዮች ምክርቤት የቀረበው ሃሰተኛ ሰነድ ከማህደር ተወግዶ በእውነተኛው ሪፖርት እንዲተካ የቀድሞው የኮሚሽኑ አባላት መንግስትን በመጠየቅ ላይ ናቸው። በ1997 ከተካሄደው አወዛጋቢ ምርጫ ጋር በተያያዘ የመንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ 193 ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ 6 ፖሊሶች ደግሞ በግጭቱ ምክንያት ሞተዋል። ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው 763 ሰዎች ሲሆኑ 71 ፖሊሶችም የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል። ከምርጫው ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች 30ሺ ሰዎች በጅምላ ታስረው ነበር። በወቅቱ ከምርጫው ጋር ተያይዞ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ለሰባት ወራት ባካሄደው ምርመራ ዜጎች በታሰሩበት እንደተገደሉና የሰውነት ክፍላቸው የተቆራረጡ እንደነበሩ ለመረዳት ችሎ ነበር። በርካቶች በሕወሃት ታጣቂዎች በዘግናኝ ሁኔታ መሰቃየታቸውን፣ጣታቸው መቆረጡንና ብዙ ግፍ መፈጸሙን አረጋግጧል። በርካታ ንብረት ከመውደሙም ሌላ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እገዳ የተጣለባቸውም ነበሩ። ኮሚሽኑ ጉዳዩን ካጣራ በኋላ መንግስት የወሰደው ርምጃ ያልተመጣጣነ መሆኑን ሕገ መንግስቱ በእጅጉ ተጥሶ በርካታ የሰብአዊ መብት ረገጣና ጅምላ ግድያዎች መፈጸማቸውን ከኮሚስኑ 10 አባላት 8 ለ 2 በሆነ ድምጽ ውሳኔ ላይ ደርሶ ነበር። ይህም ሆኖ ግን ሪፖርቱን ካዘጋጁ በኋላ ወሳኔው ለፓርላማ እንዳይቀርብና ውሳኔውን እንዲለውጡ አስገዳጅ ሁኔታ ቀርቦላቸዋል። በኮሚሽኑ አባላት ላይ ግድያና ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው ሃገር ጥለው ለመሰደድ መብቃታቸውም ነው የሚታወሰው። በምትኩ የሃሰት ሪፖርት ቀርቦ ፓርላማው በእነ አቶ መለስ ዜናዊ በሚመራው ስራ አስፈጻሚ ስልጣኑን ሲነጠቅ ትንፍሽ ያለ የምክር ቤት አባልም አልነበረም። በአሁኑ ጊዜ የለውጥ አስተዳደር ከመጣ በኋላ የቀድሞው የኮሚሽኑ አባላት ነሐሴ 28/2010 ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለሚመለከታቸው አካላት በጻፉት ደብዳቤ ቀደም ሲል በፓርላማው የጸደቀው የሃሰት ሰነድ ከማህደር ተወግዶ እውነተኛው ሪፖርት እንዲቀርብ ጠይቀው ነበር። ይህም ሆኖ ግን የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝምታን መምረጣቸው በስደት የሚገኙት የኮሚሽኑ አባላት ለኢሳት ገልጸዋል። ተቃዋሚዎችም ለሕዝብና ለፍትህ ታገልን ቢሉም ጉዳዩን ከማንሳት መቆጠባቸውን የቀድሞው የኮሚሽኑ ሰብሳቢ አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል ገልጸዋል። በምርጫ 97 ጊዜ በተፈጸመው ግድያ የጅምላ መቃብር ማየታቸውንና ይህም በሪፖርታቸው መካተቱን የሕግ ባለሙያው ዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል ያስታውሳሉ። ይሁንና እነዚህን ግድያዎችንና ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙት ሁሉ እንዳቸውም ለሕግ እንዳልቀረቡ ጨምረው ገልጸዋል።

Source: (ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 1/2011)ምርጫ 97ን ተከትሎ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች የተፈጸመውን ግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት ያጣራው ኮሚሽን አባላት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያቀረቡት ጥያቄ እስካሁን ተቀባይነት አለማግኘቱን ገለጹ። በስደት ላይ የሚገኙት የኮሚሽኑ የቀድሞ አመራሮች ከመቶ ዘጠና ዘጠኝ በላይ ሰዎች የተገደሉበትንና ከ30ሺ በላይ ሰዎች በጅምላ የታሰሩበትን እውነተኛ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማቅረብ ቢጠይቁም በመንግስት በኩል ምላሽ አላገኙም። የኮሚሽኑ አባላት እውነተኛውን ሪፖርት በወቅቱ እንዳያቀርቡ በመታገዳቸውና የግድያ ዛቻ ስለደረሰባቸው ከሃገር ተሰደው መቆየታቸው ይታወሳል። እናም ምርጫ 97ን ተከትሎ በተወካዮች ምክርቤት የቀረበው ሃሰተኛ ሰነድ ከማህደር ተወግዶ በእውነተኛው ሪፖርት እንዲተካ የቀድሞው የኮሚሽኑ አባላት መንግስትን በመጠየቅ ላይ ናቸው። በ1997 ከተካሄደው አወዛጋቢ ምርጫ ጋር በተያያዘ የመንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ 193 ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ 6 ፖሊሶች ደግሞ በግጭቱ ምክንያት ሞተዋል። ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው 763 ሰዎች ሲሆኑ 71 ፖሊሶችም የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል። ከምርጫው ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች 30ሺ ሰዎች በጅምላ ታስረው ነበር። በወቅቱ ከምርጫው ጋር ተያይዞ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ለሰባት ወራት ባካሄደው ምርመራ ዜጎች በታሰሩበት እንደተገደሉና የሰውነት ክፍላቸው የተቆራረጡ እንደነበሩ ለመረዳት ችሎ ነበር። በርካቶች በሕወሃት ታጣቂዎች በዘግናኝ ሁኔታ መሰቃየታቸውን፣ጣታቸው መቆረጡንና ብዙ ግፍ መፈጸሙን አረጋግጧል። በርካታ ንብረት ከመውደሙም ሌላ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እገዳ የተጣለባቸውም ነበሩ። ኮሚሽኑ ጉዳዩን ካጣራ በኋላ መንግስት የወሰደው ርምጃ ያልተመጣጣነ መሆኑን ሕገ መንግስቱ በእጅጉ ተጥሶ በርካታ የሰብአዊ መብት ረገጣና ጅምላ ግድያዎች መፈጸማቸውን ከኮሚስኑ 10 አባላት 8 ለ 2 በሆነ ድምጽ ውሳኔ ላይ ደርሶ ነበር። ይህም ሆኖ ግን ሪፖርቱን ካዘጋጁ በኋላ ወሳኔው ለፓርላማ እንዳይቀርብና ውሳኔውን እንዲለውጡ አስገዳጅ ሁኔታ ቀርቦላቸዋል። በኮሚሽኑ አባላት ላይ ግድያና ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው ሃገር ጥለው ለመሰደድ መብቃታቸውም ነው የሚታወሰው። በምትኩ የሃሰት ሪፖርት ቀርቦ ፓርላማው በእነ አቶ መለስ ዜናዊ በሚመራው ስራ አስፈጻሚ ስልጣኑን ሲነጠቅ ትንፍሽ ያለ የምክር ቤት አባልም አልነበረም። በአሁኑ ጊዜ የለውጥ አስተዳደር ከመጣ በኋላ የቀድሞው የኮሚሽኑ አባላት ነሐሴ 28/2010 ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለሚመለከታቸው አካላት በጻፉት ደብዳቤ ቀደም ሲል በፓርላማው የጸደቀው የሃሰት ሰነድ ከማህደር ተወግዶ እውነተኛው ሪፖርት እንዲቀርብ ጠይቀው ነበር። ይህም ሆኖ ግን የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝምታን መምረጣቸው በስደት የሚገኙት የኮሚሽኑ አባላት ለኢሳት ገልጸዋል። ተቃዋሚዎችም ለሕዝብና ለፍትህ ታገልን ቢሉም ጉዳዩን ከማንሳት መቆጠባቸውን የቀድሞው የኮሚሽኑ ሰብሳቢ አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል ገልጸዋል። በምርጫ 97 ጊዜ በተፈጸመው ግድያ የጅምላ መቃብር ማየታቸውንና ይህም በሪፖርታቸው መካተቱን የሕግ ባለሙያው ዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል ያስታውሳሉ። ይሁንና እነዚህን ግድያዎችንና ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙት ሁሉ እንዳቸውም ለሕግ እንዳልቀረቡ ጨምረው ገልጸዋል።

Welcome To All in One Entertainment Site of EthioLiveVideo for Recent Ethiopian News from Abisinia to Abyssinian with Ethiopians Musics (Musiqa) and Comedy (Comedies) including Worldwide Funny and Amazing Top Videos.
We also share a Video link of Recent Amharic Trailers or Full length Films (Movies) and Series Tv Dramas by Episode from KanaTv, Josy JTV, EBC, Fana Television FBC and EBSTV Show.

So Enjoy with us and Follow us on the above FB Link, Thanks.

Source of Additional Sites and Channels:-
Betoch Comedy Drama, Dana, Zemen, Sew Lesew, Gemena, Chilot, Neqash, Welafen, Amen, Ayer Bayer, Wazema, Mogachoch, Senselet, Meleket, Bekenat Mekakel, Bale Guday, Josy in Z House, EBC, EBSTvs Show, Kana Tv, ENN, EthSat, ZoneNiners, OMN.

Advertisements